ዜና | Oduu | News
የክላስተር3 የምግብና ጤና ነክ ብቃት ማረጋገጥ ጽ/ቤት የችግኝ መትከያ ቦታ ዝግጅት አከናወነ

የክላስተር3 የምግብና ጤና ነክ ብቃት ማረጋገጥ ጽ/ቤት ከቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመሆን የችግኝ መትከያ ቦታ ዝግጅት የጉድጓድ ቁፋሮ ስራ አከናወነ

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብ መድሃኒት ባለስልጣን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ክላስተር 3 የ2018 በጀት ዓመት የ6ወር አፈጻጸም እና በአዋጅና ደንብ እንዲሁም በመመሪያ ከጤና ፎረም፣ ከባለድርሻ አካላት፣ ከንግዱ ማህበረሰብና ከነዋሪው ጋር ዉይይት አካሄደ።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ክላስተር 3 ጽ/ቤት ኃላፊ እንደ ገለፁት ባለፉት ስድስት ወራት ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ በርካታ ስራዎች መሰራተቸውን በመግለጽ በጽ/ቤቱ የህብረተሰቡን የጤና ደህንነት ለማስጠበቅ በመደበኛ ቅድመ ብቃት ቁጥጥር እንዲሁም በዘመቻ በርካታ ስራዎች መከናወናቸዉን ጠቅሰዉ በእቅድ ከተያዙት ስራዎች በተጨማሪ ሌብነትና ብልሹ አሰራር ከመከላከል አንጻር፣ተቋማዊ ውጤታማነት በማሻሻል የሰራተኛና ተገልጋይ እርካታ ከማሳደግ አንጻር፣ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠርና አገልግሎትን ከማሻሻል አንጻር እንዲሁም የህዝብ፣ሲቪል ማኅበራትና የግል ሴክተር ተሳትፎ ስርዓትን ከማሳደግ አንፃር በ6 ወራት ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል። ‎ ባለሙያዋ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት በክላስተር ጽ/ቤቱ በወረዳው ለሚገኙ የምግብ መሸጫ እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ እንዲሁም ጤናነክ አገልግሎትና የምግብ አምራች ተቋማት ላይ ቁጥጥር በማድረግ ደረጃውን ለሚያሟሉ ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ እድሳት እና አዲስ የብቃት ማረጋገጫ ሲሰጥ እንደነበር ገልፀው ከተቋማትና ከግለሰቦች የሚመጡ ቅሬታና አቤቱታዎችን በመቀበል በርካታ ተግባራቶችን ማከናወናቸው አብራርተዋል:: በሌላ በኩል የክላስተር 1 ፅ/ቤት ቡድን አቶ አለማየሁ በትምባሆ እና አደንዛዥ እፅ ጋር በተያያዘ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በዚህም ጤናማ ፣በስነ ምግባር የታነፀ ዜጋ እንዲኖርና ንፁህ አካባቢ ለመፍጠር ማጨስ በህግ የተከለከለ መሆኑን ሁሉም በማወቅ ግንዛቤ መያዝ አለበት ብለዋል:: ‎ በመጨረሻም ባለድርሻ አካላቱ የማህበረሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ከቤቱም ለቀረቡ ሀሳቦች፣ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የክላስተር1 የጽ/ቤቱ ቡድን መሪና ባለሙያ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን አንዳንድ ቀሪ ስራዎች ያሉ መሆናቸውን በመግለጽ የባለድርሻ አካላቱ ተሳትፎና ሚና ወሳኝ መሆኑን ገለጸው በቀጣይነት በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ አቅጣጫ በማስቀመጥ የጥቆማ ነጻ 8864 ላይ ጥቆማ በመስጠት እንደሚቻል በመግለጽ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ መድረኩ ተጠናቋል:: ‎

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የክላስተር 3 የምግብና ጤና ነክ ተቋማት የብቃት ማረገጥ ጽ/ቤት የብቃት እና የእድሳት ስራን በኦላይን ለማግኘት አገልግሎትን አሰጣጡን የሚያግዝ በዲጅታል አገልግሎት መረብ መጀመሩን ጽ/ቤቱ አስተዋወቀ

በአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒት ባለስልጣን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የክላስተር -3 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የምግብና ጤና ነክ ተቋማት የብቃት መረጋገጫ ፍቃድን በኦላይን ለማግኝት እና ለመመዝገብ የሚያግዝ የምግብና መድሃኒት የዲጅታል አገልግሎት መረብ አስተዋወቀ ፡፡ ተቋማት አዲስ የብቃት ማረጋገጫ ለመዉሰድ ፣ለማደስ እንዲሁም ምዝገባዎችን ለማከነወን የዲጅታል አገልግሎት መረብ መጠቀማቸዉ አገልግሎት ለማግኘት ወደ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በአካል ሲመጡ የሚወስድባቸው ጊዜና የሚያወጡት ገንዘብ በማስቀረት በተቀላጠፈና ስታንዳርዱን በጠበቀ መልኩ አገልግሎት እንዲያገኙ እገዛዉ የጎላ ነዉ ሲሉ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የክላስተር -3 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ነፃነት ገ/ፃድቃን ተነግሯል ። በመርሃ-ግብሩ ላይ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የክላስተር -3 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የጤናና ጤና ነክ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ብቃት መረጋገጫ ቡድን መሪ አቶ አለመየሁ ወርቁ እንደገለጹት ነዋሪዎች በቀላሉ ባሉበት ቦታ ሆነው የምግብና ጤና ነክ ተቋማት የብቃት መረጋገጫ ፍቃድን በኦላይን ለማግኝት እና ለመመዝገብ የምግብና መድሃኒት የዲጅታል አገልግሎት መረብ መጠቀመም ይቻላል ብለዋል ፡፡ ከዚህም ጋር አያይዘዉ የብቃት ማረጋገጫ አገልግሎት አሰጣጥ ለማግኝት የዲጅታል አገልግሎት መረብ ላይ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች፡-የአንድ ድርጅት መመስረቻ ሰነድ፣የታደስ የንግድ ፍቃድ ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NUMBERር/፣የቦታዉ ካርታ ወይም የኪራይ ዉል ስምምነት የጽ/ቤቱን የዲጅታል ስርዓ ተጠቅሞ መመዝገብ እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡ የጽ/ቤቱን የድረ -ገጽ አገልግሎት ለማግኛት እና ዝርዝር መመሪያዎችን ለማንበብ ወደ www.aafdanslc3.gov.et ድር ገጽ ጎራ ይበሉ ሲሉ አስተዋዉቀዋል፡፡

image
image
image
image